Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) - ኢሰመኮ

Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) - ኢሰመኮ

Non-profit Organizations

Promote and ensure the protection of human rights for all

About us

Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) is an independent federal state body established as per the Federal Constitution and reporting to the House of People’s Representatives as a national human rights institution with the mandate for the promotion and protection of human rights. (Article 55/14 of FDRE Constitution cum Proclamation No. 210/2000, as amended by Proclamation No. 1224/2020)

Website
http://ehrc.org
Industry
Non-profit Organizations
Company size
201-500 employees
Headquarters
Addis Ababa
Type
Nonprofit

Locations

Employees at Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) - ኢሰመኮ

Updates

  • በክልል ደረጃ ሲካሄድ የቆየው 4ኛው ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች ምስለ ችሎት ውድድር ተጠናቀቀ ... የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለ4ኛ ጊዜ እያካሄደ ባለው ዓመታዊ ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች ምስለ ችሎት ውድድር የመጀመሪያው ምዕራፍ ውድድር ተጠናቀቀ፡፡ ውድድሩ በ12 ክልሎች እና በ2 ከተማ አስተዳደሮች የተካሄደ ሲሆን ከ81 ትምህርት ቤቶች 162 ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ተማሪዎቹ የመከራከሪያ ጽሑፋቸውን በማዘጋጀት የመወዳደሪያ መስፈርቱን ያሟሉ ሲሆን ሚያዝያ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. የቃል ክርክር አካሂደዋል፡፡ በኢሰመኮ አዘጋጅነት በየዓመቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች የምስለ ችሎት ውድድር ምናባዊ በሆነ የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ (hypothetical case) ላይ ተማሪዎች የአመልካች እና የተጠሪ ወገንን በመወከል የጽሑፍ እና የቃል ክርክር የሚያደርጉበት ሲሆን የመደበኛ ፍርድ ቤት የክርክር ሥርዓትን የሚከተል ሆኖ በተወዳዳሪ ተማሪዎች እና በትምህርት ቤቶች ማኅበረሰብ ዘንድ የሰብአዊ መብቶች ዕውቀትንና ክህሎትን ለመገንባት ያለመ ነው፡፡ በክልል ደረጃ በተካሄደ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች ምስለ ችሎት ውድድር የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት (ከኦሮሚያ ክልል)፣ አባ ፖስካል ትምህርት ቤት (ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል)፣ ሊች ጎጎ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ከማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል)፣ ዳዕሮ አካዳሚ (ከትግራይ ክልል)፣ ሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር)፣ እቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት (ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር)፣ ጅግጅጋ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ከሶማሊ ክልል)፣ አሶሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል)፣ ዱፕቲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ከአፋር ክልል)፣ ሪስፕንስ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት (ከአማራ ክልል)፣ ቢሻው ወልደዮሃንስ ሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት (ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል)፣ ቅዱስ ገብርኤል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ከሲዳማ ክልል)፣ ማሪፍ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት (ከሐረሪ ክልል) እና ኤላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ከጋምቤላ ክልል) አሸናፊ ሆነዋል፡፡ ውድድሩን በበላይነት ካጠናቀቁት 14 ትምህርት ቤቶች መካከል በጽሑፍ ክርክር የላቀ ነጥብ የሚያስመዘግቡ 8 ቡድኖች በግንቦት ወር በአዲስ አባባ ከተማ በሚካሄደው ሀገር አቀፍ ውድድር ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ የዚህ ዓመት ምናባዊ ጉዳይ ወቅታዊ በሆነው በሽግግር ፍትሕ ሂደት ላይ ያተኮረ ሲሆን ታሳቢ ሊደረጉ የሚገቡ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮችን በማንሳት የተወዳዳሪ ተማሪዎችን እና የትምህርት ቤቶች ማኅበረሰብን ዕውቀትና ግንዛቤ ለመገንባት ዕድል የሚፈጥር ነው፡፡ በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ። #Ethiopia #HumanRightsForAll

    በክልል ደረጃ ሲካሄድ የቆየው 4ኛው ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች ምስለ ችሎት ውድድር ተጠናቀቀ - Ethiopian Human Rights Commission - EHRC

    በክልል ደረጃ ሲካሄድ የቆየው 4ኛው ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች ምስለ ችሎት ውድድር ተጠናቀቀ - Ethiopian Human Rights Commission - EHRC

    https://ehrc.org

  • ጋምቤላ:- ከግንቦት 2015 ዓ.ም. አንስቶ በተከሰቱ ግጭቶች ላይ በተከናወነ ምርመራ ግኝቶችና ምክረ ሐሳቦች ላይ ውይይት ተካሄደ ... የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጋምቤላ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ ወቅቶች በተከሰቱ ግጭቶች እና የጸጥታ መደፍረስ ሁኔታዎች ሳቢያ የደረሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ የተደረገ የምርመራ ሪፖርት የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ኮሚሽኑ በምርመራ ሪፖርቱ በተለዩ ግኝቶችና በተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. በጋምቤላ ከተማ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ የኮሚሽኑ፣ የፌዴራል መንግሥት እና የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል። በውይይቱ ኮሚሽኑ በጋምቤላ ክልል በጎግ ወረዳ፣ በጋምቤላ ወረዳ፣ በኢታንግ ልዩ ወረዳ አቹዋ ቀበሌ፣ ፒኖ ንዑስ ቀበሌ፣ እንዲሁም ቴምፒኝ መንደር እና በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶችና ጥቃቶች የተነሳ በተፈጸሙ ግድያዎች፤ በደረሱ የአካል ጉዳቶች፤ የንብረት ውድመቶች እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ባከናወነው ምርመራ የተለዩ ግኝቶችና የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ለተሳታፊዎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል። እንዲሁም በክልሉ በሚገኙ ስደተኞች እና ተቀባይ ማኅበረሰብ ላይ የደረሱ ጉዳቶች በውይይቱ የቀረቡ ሲሆን መሰል ችግሮች በቀጣይ እንዳይከሰቱ በሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ መከናወን በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል። የውይይቱ ተሳታፊዎች ኮሚሽኑ በክልሉ ተከስተው በነበሩ ግጭቶችና በተፈጸሙ ጥቃቶች ላይ ባከናወነው ምርመራ የለያቸው ግኝቶችና ያቀረባቸው ምክረ ሐሳቦች የችግሮቹን ስፋትና ነባራዊ ሁኔታ የሚያሳዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በክልሉ በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ግጭቶች መንስኤዎች ላይ ኮሚሽኑ ተጨማሪ ጥናት እና ምርመራዎችን እንዲያደረግ እንዲሁም የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች እንዲፈጸሙ በቅርበት እንዲከታተል ጠይቀዋል። በውይይቱ ኮሚሽኑ የምርመራ ሪፖርቱን ይፋ ካደረገ በኋላ በክልሉ መንግሥት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ተገቢ እና አበረታች መሆናቸውን የገለጸ ሲሆን በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶችና ጥቃቶች አሁንም በመቀጠላቸው በክልሉ የሚገኙ የጸጥታ መዋቅሮችን በመፈተሽ ብቁ፣ ሚዛናዊ እና ግጭቶችን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማረጋጋት የሚያስችላቸውን ዐቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ ምክረ ሐሳብ አቅርቧል። በተጨማሪም በስደተኞች እና በተቀባይ ማኅበረሰብ መካከል ያሉ አለመግባባቶች እና ያለመግባባት ምክንያቶች በዘላቂነት የሚፈቱበትን መንገድ ለመፍጠር የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጥረቶችን ሊያደርጉ እንደሚገባ ጠቁሟል። በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ። #Ethiopia #Gambella #HumanRightsForAll

    ጋምቤላ:- ከግንቦት 2015 ዓ.ም. አንስቶ በተከሰቱ ግጭቶች ላይ በተከናወነ ምርመራ ግኝቶችና ምክረ ሐሳቦች ላይ ውይይት ተካሄደ - Ethiopian Human Rights Commission - EHRC

    ጋምቤላ:- ከግንቦት 2015 ዓ.ም. አንስቶ በተከሰቱ ግጭቶች ላይ በተከናወነ ምርመራ ግኝቶችና ምክረ ሐሳቦች ላይ ውይይት ተካሄደ - Ethiopian Human Rights Commission - EHRC

    https://ehrc.org

  • ጋምቤላ:- ከግንቦት 2015 ዓ.ም. አንስቶ በተከሰቱ ግጭቶች ላይ በተከናወነ ምርመራ ግኝቶችና ምክረ ሐሳቦች ላይ ውይይት ተካሄደ ... የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጋምቤላ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ ወቅቶች በተከሰቱ ግጭቶች እና የጸጥታ መደፍረስ ሁኔታዎች ሳቢያ የደረሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ የተደረገ የምርመራ ሪፖርት የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ኮሚሽኑ በምርመራ ሪፖርቱ በተለዩ ግኝቶችና በተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. በጋምቤላ ከተማ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ የኮሚሽኑ፣ የፌዴራል መንግሥት እና የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል። በውይይቱ ኮሚሽኑ በጋምቤላ ክልል በጎግ ወረዳ፣ በጋምቤላ ወረዳ፣ በኢታንግ ልዩ ወረዳ አቹዋ ቀበሌ፣ ፒኖ ንዑስ ቀበሌ፣ እንዲሁም ቴምፒኝ መንደር እና በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶችና ጥቃቶች የተነሳ በተፈጸሙ ግድያዎች፤ በደረሱ የአካል ጉዳቶች፤ የንብረት ውድመቶች እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ባከናወነው ምርመራ የተለዩ ግኝቶችና የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ለተሳታፊዎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል። እንዲሁም በክልሉ በሚገኙ ስደተኞች እና ተቀባይ ማኅበረሰብ ላይ የደረሱ ጉዳቶች በውይይቱ የቀረቡ ሲሆን መሰል ችግሮች በቀጣይ እንዳይከሰቱ በሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ መከናወን በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል። የውይይቱ ተሳታፊዎች ኮሚሽኑ በክልሉ ተከስተው በነበሩ ግጭቶችና በተፈጸሙ ጥቃቶች ላይ ባከናወነው ምርመራ የለያቸው ግኝቶችና ያቀረባቸው ምክረ ሐሳቦች የችግሮቹን ስፋትና ነባራዊ ሁኔታ የሚያሳዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በክልሉ በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ግጭቶች መንስኤዎች ላይ ኮሚሽኑ ተጨማሪ ጥናት እና ምርመራዎችን እንዲያደረግ እንዲሁም የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች እንዲፈጸሙ በቅርበት እንዲከታተል ጠይቀዋል። በውይይቱ ኮሚሽኑ የምርመራ ሪፖርቱን ይፋ ካደረገ በኋላ በክልሉ መንግሥት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ተገቢ እና አበረታች መሆናቸውን የገለጸ ሲሆን በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶችና ጥቃቶች አሁንም በመቀጠላቸው በክልሉ የሚገኙ የጸጥታ መዋቅሮችን በመፈተሽ ብቁ፣ ሚዛናዊ እና ግጭቶችን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማረጋጋት የሚያስችላቸውን ዐቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ ምክረ ሐሳብ አቅርቧል። በተጨማሪም በስደተኞች እና በተቀባይ ማኅበረሰብ መካከል ያሉ አለመግባባቶች እና ያለመግባባት ምክንያቶች በዘላቂነት የሚፈቱበትን መንገድ ለመፍጠር የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጥረቶችን ሊያደርጉ እንደሚገባ ጠቁማል። #Ethiopia #HumanRightsForAll #Gambella https://ehrc.org/?p=27862 በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

    ጋምቤላ:- ከግንቦት 2015 ዓ.ም. አንስቶ በተከሰቱ ግጭቶች ላይ በተከናወነ ምርመራ ግኝቶችና ምክረ ሐሳቦች ላይ ውይይት ተካሄደ - Ethiopian Human Rights Commission - EHRC

    ጋምቤላ:- ከግንቦት 2015 ዓ.ም. አንስቶ በተከሰቱ ግጭቶች ላይ በተከናወነ ምርመራ ግኝቶችና ምክረ ሐሳቦች ላይ ውይይት ተካሄደ - Ethiopian Human Rights Commission - EHRC

    https://ehrc.org

  • Exchange of Ideas and Expertise among African NHRIs Fuels Regional Cooperation on Human Rights ... The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) hosted a networking event for National Human Rights Institutions (NHRIs) from Africa on April 22, 2024, at its head office in Addis Ababa. The gathering held on the sidelines of the Tenth Session of the Africa Regional Forum on Sustainable Development brought together a group of representatives from NHRIs of Cameroon, Ghana, Kenya, Malawi, Sierra Leone, and South Africa. Additionally, representatives from the Danish Institute for Human Rights (DIHR) and the Network of African National Human Rights Institutions (NANHRI) participated, promoting a comprehensive and collaborative environment. Designed to spark dialogue and inspire creative approaches, the event featured a captivating photography exhibition showcasing entries from EHRC’s Third Annual Human Rights Film Festival photography competition. This unique display served as a springboard for discussion, inspiring creative approaches to human rights advocacy. It also facilitated a sense of cultural exchange and camaraderie among participants. The impact of the Human Rights Film Festival resonated with attendees. Participants expressed their appreciation for the festival’s innovative approach to raising awareness about critical human rights issues. Discussions revealed a strong interest in replicating similar initiatives, with some participants exploring the possibility of collaboration with the EHRC to implement such programs in their own countries, cultivating a promising path for broader regional impact. EHRC’s Deputy Chief Commissioner, Rakeb Messele, delivered opening remarks that underscored the Commission’s experience in organizing the annual human rights film festival. Rakeb emphasized the importance of fostering stronger collaboration and coordination between NHRIs, highlighting the potential for collective action to advance human rights across Africa. በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ። #Ethiopia #HumanRightsForAll

    Exchange of Ideas and Expertise among African NHRIs Fuels Regional Cooperation on Human Rights - Ethiopian Human Rights Commission - EHRC

    Exchange of Ideas and Expertise among African NHRIs Fuels Regional Cooperation on Human Rights - Ethiopian Human Rights Commission - EHRC

    https://ehrc.org

  • የሳምንቱ #HumanRights Concept: ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የሥራ አካባቢ የዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት ስምምነት ቁጥር 155 – የሥራ ላይ ደኅንነት እና ጤና ስምምነት፣ አንቀጽ 16 - አሠሪዎች በቁጥጥራቸው ሥር ያሉ የሥራ ቦታዎች፣ ማሽኖች፣ መሣሪያዎች እና የአሠራር ሂደቶች ምክንያታዊና ተግባራዊ ሊሆን በሚችለው መጠን ደኅንነታቸው የተጠበቀ እና ምንም የጤና ሥጋት የማያስከትሉ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ ሊደረጉ ይገባል፤ - አሠሪዎች ተገቢውን የመከላከያ እርምጃ ሲወስዱ፣ በቁጥጥራቸው ሥር ያሉ ኬሚካላዊ፣ ቁሳዊ እና ሥነ-ሕይወታዊ ንጥረ-ነገሮች እና መሣሪያዎች ምክንያታዊና ተግባራዊ ሊሆን በሚችለው መጠን ለጤና አደጋ የሌላቸው መሆኑን እንዲያረጋግጡ ሊደረጉ ይገባል፤ - የአደጋ ሥጋትን ወይም አሉታዊ የጤና ተጽዕኖዎችን ምክንያታዊና ተግባራዊ ሊሆን በሚችለው መጠን ለመከላከል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አሠሪዎች በቂ የደኅንነት መጠበቂያ ልብሶችንና መሣሪያዎችን እንዲያቀርቡ ሊደረጉ ይገባል። በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ። 🔗 https://ehrc.org/?p=27779 #Ethiopia #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

  • “የኢሰመኮ-ሲቪል ማኅበራት የትብብር መድረክ”ን ከኢሰመኮ ጋር የሚመሩ ተባባሪ መሪ (Co-chair) እና ምክትል ተባባሪ መሪ (V/Co-chair) ተመረጡ ... የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሲቪል ማኅበራት ጋር በትብብር እና በቅንጅት ለመሥራት ያቋቋመው “የኢሰመኮ-ሲቪል ማኅበራት ትብብር መድረክ” የተለያዩ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኃላፊዎችና ተወካዮች የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. በኮሚሽኑ ዋና ጽሕፈት ቤት አካሂዷል፡፡  የውይይቱ ዋና ዓላማ የትብብር መድረኩን ለማጠናከርና ወደላቀ ተግባር ለማሸጋገር ይቻል ዘንድ የሥራ እንቅስቃሴውን መገምገም እንዲሁም የትብብር መድረኩን ከኢሰመኮ ጋር የሚመሩ ተባባሪ መሪ (Co-chair) እና የተቋቋሙትን ንዑሳን የትብብር ቡድኖች የሚያስተባብር ምክትል ተባባሪ መሪ (V/Co-chair) የሲቪል ማኅበራት ተወካዮችን መምረጥ ነው፡፡ በውይይት መድረኩ ኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶችን ሁኔታ ለማሻሻል ከሚከተላቸው ስልቶች መካከል ከሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ጋር በትብብር መሥራት አንዱ በመሆኑ ‘’የኢሰመኮ-ሲቪል ማኅበራት የትብብር መድረክ” ነሐሴ 18 ቀን 2013 ዓ.ም. በይፋ መቋቋሙ ተገልጿል፡፡ የትብብር መድረኩ ከተቋቋመ ጀምሮ የተከናወኑ ተግባራትና አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን በቀጣይ የትብብር መድረኩን አጠናክሮ መሄድ አስፈላጊ እንደሆነም ተሰምሮበታል። ተሳታፊዎች የትብብር መድረኩ ለሰብአዊ መብቶች ጥበቃ መሻሻልና መስፋፋት የሚረዱ ተግባራትን በተሻለ መልኩ እንዲያከናውን የሚያግዙ የትኩረት አቅጣጫዎች፣ መዋቅራዊ የሰብአዊ መብቶች ተግዳሮቶች እና ጭብጦችን ለመለየት በጋራ የሚሠራበት ምልከታ ላይ ተወያይተዋል። በ2015 ዓ.ም. የተቋቋሙ ንዑሳን የትብብር ቡድኖች ሊጠናከሩ የሚችሉበት ሐሳቦችንም አቅርበዋል፡፡ በመጨረሻም በተሻሻለው የትብብር መድረኩ የጋራ መግባቢያ ሰነድ (TOR) መሠረት የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች እና የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት ለሚቀጥለው 1 ዓመት የትብብር መድረኩ ተባባሪ መሪ እና ምክትል ተባባሪ መሪ ሆነው እንዲያገለግሉ የውይይቱ ተሳታፊዎች መርጠዋል፡፡ የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የሲቪል ማኅበራት ከኮሚሽኑ ጋር የሚያደርጉት ትብብርና ቅንጅት ለሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ማሻሻልና ማስፋፋት ሥራ ትልቅ አንድምታ እንዳለው ገልጸዋል። ለትብብር መድረኩ ውጤታማነትም የሁሉም አባል ሲቪል ማኅበራት ተሳትፎ እና ቁርጠኛ የሆኑ የሲቪል ማኅበራት ተወካዮች እንደሚያስፈልጉ አስገንዝበዋል። በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ። #Ethiopia #HumanRightsForAll

    “የኢሰመኮ-ሲቪል ማኅበራት የትብብር መድረክ”ን ከኢሰመኮ ጋር የሚመሩ ተባባሪ መሪ (Co-chair) እና ምክትል ተባባሪ መሪ (V/Co-chair) ተመረጡ - Ethiopian Human Rights Commission - EHRC

    “የኢሰመኮ-ሲቪል ማኅበራት የትብብር መድረክ”ን ከኢሰመኮ ጋር የሚመሩ ተባባሪ መሪ (Co-chair) እና ምክትል ተባባሪ መሪ (V/Co-chair) ተመረጡ - Ethiopian Human Rights Commission - EHRC

    https://ehrc.org

  • ምን? - የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች እና ሕፃናት ኮሚሽነር ለመጠቆም የወጣ የሕዝብ ማስታወቂያ እንዴት? - ጥቆማ አቅራቢዎች ይህንን የተያያዘውን ቅጽ በመሙላት https://shorturl.at/deruM የሚከተሉትን የጥቆማ ማቅረቢያ መንገዶች በመጠቀም ጥቆማቸውን መላክ ይችላሉ፡፡ * በኢሜል አድራሻችን፦ HumanrightNC@hopr.gov.et * በቴሌግራምና በዋትስ-አፕ ስልክ ቁጥር፡- 09-69-27-43-43 * የመልእክት ሳጥን ቁጥር:- 80001 * በአካል ማቅረብ ለሚፈልጉ፦ አራት ኪሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የእንግዳ መቀበያ ቢሮ በተዘጋጀው ዝግ ሳጥን ውስጥ የጥቆማ ወረቀታቸውን ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጥቆማ ጊዜው እስከ ማክሰኞ ሚያዝያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. 🔗 https://lnkd.in/eEvTFK5R #Ethiopia #HumanRightsForAll

    • የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች እና ሕፃናት ኮሚሽነር ለመጠቆም የወጣ የሕዝብ ማስታወቂያ
  • ሕፃናትን ለውትድርና መመልመል (ማብራሪያ) ... ሕፃን ወታደሮች፣ ሕፃናትን በጦርነት ወይም በግጭት ውስጥ ማሳተፍ ምን ማለት ነው? ዓለም አቀፉ የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ የአፍሪካ የሕፃናት መብቶች እና ደኀንነት ቻርተር እንዲሁም ሕፃናትን በትጥቅ ግጭቶች ውስጥ ማሳተፍን በተመለከተ የወጣው ዓለም አቀፉ የሕፃናት መብቶች ስምምነት አማራጭ ፕሮቶኮል (Optional Protocol to the Convention on the Rights of the Child on the Involvement of Children in Armed Conflict) ከ18 ዓመት በታች የሆነ ማንኛውም ሰው ሕፃን እንደሚባል ይደነግጋሉ። የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የሕፃናትን የዕድሜ ወሰን በግልጽ ባያስቀምጥም እነዚህን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ኢትዮጵያ ፈርማ ያጸደቀች በመሆኗ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 9(4) መሠረት የሀገሪቱ ሕግ አካል ናቸው። ስለሆነም በኢትዮጵያም ከ18 ዓመት በታች የሆነ ማንኛውም ሰው ሕፃን ይባላል። ሕፃን ወታደሮችን የሚመለከቱ የተለያዩ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ስምምነቶችና ሕጎች ቢኖሩም ሕፃን ወታደሮች ማለት ምን ማለት ነው ለሚለው ግን ትርጉም አይሰጡም፡፡ ከጦር ኃይሎች ወይም ከታጠቁ ቡድኖች ጋር ተሳትፎ ያላቸውን ሕፃናት አስመልክቶ የወጣው የፓሪስ መርሖዎችና መመሪያዎች፣ ሕፃናት ወታደሮች ወይም ሕፃናትን በጦርነት ወይም በግጭት ውስጥ ማሳተፍ ማለት አንድን ሕፃን በመከላከያ ወይም በታጠቁ ቡድኖች በማናቸውም መንገድ ለውትድርና አገልግሎት መመልመልን ወይም በምግብ አብሳይነት ወይም አቅራቢነት፣ በሰላይነት፣ በመልዕክተኛነት፣ በወሲብ ብዝበዛ ድርጊት እና በሌሎች መሰል ተግባራት ላይ እንዲሳተፉ ማድረግን እንደሚያጠቃልል ያስቀምጣል፡፡ ይህም የሚገልጸው በግጭት ውስጥ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላቸውን ብቻ ሳይሆን ቀጥተኛ ተሳትፎ የሌላቸውንም ሕፃናት እንደሚያካትት ነው። ተፈጻሚነት ያላቸው ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ የሕግ ማዕቀፎች የትኞቹ ናቸው? ዓለም አቀፍ የሕግ ማዕቀፎች ዓለም አቀፍ የሕፃናት መብቶች ስምምነት የሕፃናት መብቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደነግግ ስምምነት ነው፡፡ ስምምነቱ ሀገራት ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች በጦርነት ውስጥ በቀጥታ ተካፋይ እንዳይሆኑ የተቻላቸውን እርምጃ ሊወስዱ እና ለጦር ኃይላቸው ከመመልመል ሊታቀቡ እንደሚገባ ይደነግጋል። ዕድሜያቸው በ15 እና በ18 ዓመት መካከል ያሉትንም ሲመለምሉ በዕድሜያቸው ከፍ ላሉት ቅድሚያ መስጠት እንዲሁም በጦርነት ወይም ግጭት ወቅት ሀገራት በራሳቸው ላይ ተፈጻሚነትና ለሕፃናት አግባብነት ያላቸው ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕጎች እና ደንቦች ማክበርና መከበራቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው ያስገነዝባል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1949 ሲቪል ሰዎችን በጦርነት ጊዜ ለመጠበቅ የወጣው የጄኔቫ ስምምነት ሕፃናት በጦርነት ወቅት ጥበቃ ከሚደረግላቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች መካከል መሆናቸውን እና ማንኛውም አካል በወታደርነትና በሌሎች የውትድርና አገልግሎት ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ እንደሌለበት ይደነግጋል፡፡ የጄኔቫ ስምምነቶችን ተከትሎ ዓለም አቀፍ የትጥቅ ግጭቶች ጉዳተኞችን ለመጠበቅ የወጣው የጄኔቫ ስምምነቶች ተጨማሪ ፕሮቶኮል1 ቁጥር 1 ሕፃናት በተለይም በወታደርነት እንዳይመለመሉ ተፋላሚ ኃይሎች የሚችሉትን ማናቸውንም እርምጃዎች መውሰድ እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ዓለም አቀፍ ያልሆኑ የትጥቅ ግጭቶች ጉዳተኞችን ለመጠበቅ የወጣው የጄኔቫ ስምምነቶች ተጨማሪ ፕሮቶኮል2 ቁጥር 2 በተመሳሳይ ሁኔታ ሕፃናትን ለውትድርና መመልመልን ይከለክላል፡፡ ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ 🔗 https://ehrc.org/?p=27746 በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ። #Ethiopia #HumanRightsForAll

    ሕፃናትን ለውትድርና መመልመል - Ethiopian Human Rights Commission - EHRC

    ሕፃናትን ለውትድርና መመልመል - Ethiopian Human Rights Commission - EHRC

    https://ehrc.org

  • የሴቶችና ሕፃናት ሁለተኛ ደረጃ ጥቃት (ማብራሪያ) ... ሁለተኛ ደረጃ ጥቃት ምንድነው? የጥቃት ተጎጂዎች ለደረሰባቸው አካላዊ፣ ጾታዊ፣ ወሲባዊ ወዘተ. ጥቃት የሕግ፣ የጤና፣ የማኅበራዊና ሥነ-ልቦናዊ ድጋፍ እና መፍትሔ ለማግኘት በሚያደርጉት ጥረት በማኅበረሰቡ፣ በአገልግሎት ሰጪ ሰዎች ወይም በተቋማት ተጨማሪ ጉዳትና ጥቃት ሲደርስባቸው ሁለተኛ ደረጃ ጥቃት (Secondary Victimization) ወይም ድርብ ጥቃት (Double victimization) ወይም ድኅረ-ወንጀል ጥቃት (Post crime victimization) ይባላል፡፡ ሁለተኛ ደረጃ ጥቃት በመጀመሪያ ደረጃ ጥቃት አማካኝነት የደረሰውን ጉዳት የሚያባብስ ሲሆን፣ በተጎጂዎች የማገገም፣ መልሶ የመቋቋም፣ ፍትሕ እና ውጤታማ መፍትሔ የማግኘት እንዲሁም የመዳን ዐቅም ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ አለው፡፡ ሁለተኛ ደረጃ ጥቃት ከመጀመሪያ ደረጃ ጥቃት በምን ይለያል? የመጀመሪያ ደረጃ ጥቃት እና የሁለተኛ ደረጃ ጥቃት ልዩነት በጥቃቱ ዐይነት፣ በጥቃቱ ምንጭ እንዲሁም ጥቃቱ በሚደርስበት ጊዜ ተከፋፍሎ ሊታይ ይችላል። የመጀመሪያ ደረጃ ጥቃት በተጎጂ ላይ ከተፈጸመው የወንጀል ድርጊት በቀጥታ የሚመነጩ አካላዊ፣ ወሲባዊ፣ ሥነ-ልቦናዊ፣ ስሜታዊ እና የመሳሰሉትን ጥቃቶች ያጠቃልላል፡፡ ሁለተኛ ደረጃ ጥቃት ከመጀመሪያ ደረጃው ጥቃት ጋር የተያያዘ ቢሆንም፣ በወንጀል ድርጊቱ ቀጥተኛ ውጤት ሳይሆን ሰዎች እና ተቋማት ምላሽ በሚሰጡበት ጊዜ በተጎጂ ላይ የሚያደርሱትን ተጨማሪ ስቃይና እንግልት የሚያመለክት ነው። ሆኖም፣ ከመጀመሪያ ደረጃ ጥቃት ጋር ተያያዥነት ያለው በመሆኑ ራሱን ችሎ ከሚፈጸም አዲስ እና የተለየ ጥቃት (new and separate incident) ይለያል። በመጀመሪያ ደረጃ ጥቃት የጉዳቱ ምንጭ በተጎጂ ላይ የወንጀል ድርጊቱን ወይም ጥቃቱን የፈጸመው ሰው ሲሆን፣ ሁለተኛ ደረጃ ጥቃት ግን በተጎጂ ቤተሰቦች፣ ጓደኞች፣ የሙያ ባልደረቦችና በአካባቢው ማኅበረሰብ ወይም ለጉዳት ምላሽ ለመስጠት በተቋቋሙ የፍትሕ እና የጤና ተቋማት ወይም ባለሞያዎች ወይም የተጎጂን ጉዳት፣ ክብርና ፍላጎት ያላገናዘበ ዘገባ በሚያሰራጩ መገናኛ ብዙኃን ሊፈጸም ይችላል። ከጊዜ አንጻር፣ የመጀመሪያ ደረጃ ጥቃት የወንጀል ድርጊቱ ወይም ቀዳሚው ጥቃት በደረሰበት ጊዜና ቅጽበት የሚከሰት ሲሆን፣ ሁለተኛ ደረጃ ጥቃት ግን የመጀመሪያው ጥቃት ከደረሰ በኋላ ለምሳሌ ተጎጂዎች የደረሰባቸውን ጉዳት ለቅርብ ቤተሰብ ወይም ጓደኛ በሚያስረዱበት ጊዜ ወይም በፍትሕ አስተዳደር ሂደት ውስጥ በአቤቱታ አቀራረብ፣ በምርመራ፣ በክስ አቀራረብና አሰማም እንዲሁም በድኅረ ችሎት ሂደቶች፣ በተቀናጀ የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ማእከላት ወይም በመጠለያ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ውስጥ በሚያልፉበት ጊዜ ሊከሰት የሚችል ነው፡፡ በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚደርስ ሁለተኛ ደረጃ ጥቃት መገለጫዎች ምንድን ናቸው? ማንኛውም የጥቃት ተጎጂ የሆነ ሰው ሁለተኛ ደረጃ ጥቃት ሊደርስበት ይችላል። ሆኖም የተወሰኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ለሁለተኛ ደረጃ ጥቃት ከፍ ያለ ተጋላጭነት ያላቸው ሲሆን በተለይም ሴቶች እና ሕፃናት በዚህ ውስጥ ይካተታሉ። በወንጀል ዐይነት ተለይቶ ሲታይም የአካላዊ ጥቃት፣ የወሲባዊ እና ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት፣ እንደዚሁም በቤት ውስጥ የሚፈጸም ጥቃት ሰለባዎች ከሌሎች የወንጀል ዐይነቶች ተጎጂዎች በበለጠ ሁኔታ ለሁለተኛ ደረጃ ጥቃት ተጋላጭነት አላቸው። ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ 🔗 https://ehrc.org/?p=27739 በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ። #Ethiopia #HumanRightsForAll

    የሴቶችና ሕፃናት ሁለተኛ ደረጃ ጥቃት - Ethiopian Human Rights Commission - EHRC

    የሴቶችና ሕፃናት ሁለተኛ ደረጃ ጥቃት - Ethiopian Human Rights Commission - EHRC

    https://ehrc.org

  • የሳምንቱ #HumanRights Concept: በፕሮጀክቶች ምክንያት የሚከሰቱ መፈናቀሎች በአፍሪካ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃ እና ድጋፍን አስመልክቶ የተደረገ የአፍሪካ ኅብረት ስምምነት (የካምፓላ ስምምነት)፣ አንቀጽ 10 - ተዋዋይ ሀገራት በተቻለ መጠን በሕዝባዊ ወይም በግል አካላት በሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ምክንያት የሚፈጠርን መፈናቀል መከላከል አለባቸው፤  - ተዋዋይ ሀገራት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በፕሮጀክቶቹ ሊፈናቀሉ ከሚችሉ ሰዎች ጋር ሙሉ መረጃ በመለዋወጥና ምክክር በማድረግ አዋጭ የሆኑ አማራጮችን ማጤናቸውን ያረጋግጣሉ፤  - ተዋዋይ ሀገራት አንድ የቀረበ የልማት ፕሮጀክት ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት የማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ተጽዕኖ ግምገማ ያካሂዳሉ፡፡ በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ። 🔗 https://ehrc.org/?p=27671 #Ethiopia #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

Similar pages

Browse jobs